በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብዕ ኮሌጅ መምህራን፣ተማሪዎችና የአስተዳደር ሰራተኞች በልዩ ልዩ ሀሳቦች የተሳተፉበት “ሰበዝ” መጽሔት ቁጥር ፪ ዕትም ሰኔ 29/2014 ዓ.ም በማራኪ አልሙኒዬም ህንፃ የመሰብሰቢያ አዳራሽ የዩኒቨርስቲያችን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የምረቃ ሥነሥርዓት ተካሂድል፡፡
በመርሃ ግብሩ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት
አፀደወይንን ጨምሮ የአካዳሚክ ም/ፕሬዚዳንት ዶ/ር ካሳሁን ተገኘ፣ የማህበራዊ ሳይንስና ሥነ-ሰብዕ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር አገኘሁ ተስፋ፣የአማራ ክልል የባህል ማዕከል ዋና ዳሬክተር አቶ ገ/ማሪያም ይርጋ፣ መምህራንና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡
የኮሌጁ ም/ዲን ዶ/ር አዕምሮ አስማማው መርሃ ግብሩነ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ከከፈቱ በኋላ የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አሥራት አፀደወይን የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡ በንግግራቸወም ኮሌጁ ከዚህ ቀደም በኪነ-ጥበብ፣ በታሪክ፣ በባህል፣ በማህበራዊና በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረጉ ሴሚናሮችንና አውደጥናቶችን በተከታታይ በማካሄድ ኮሌጀጁ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ ኮሌጁ በየዓመቱ ሰበዝ መጽሄትን ማዘጋጀቱ ለቀጣይ ትውልድ አበረታች መሆኑንና ህትመቱ ቀጣይነት እንዲኖረው ያሳሰቡ ሲሆን ወደፊትም በዩኒቨርሳቲው የማህበረሰብ ሬዲዮ እንዲመሰረት የኮሌጁ መምህራንና ሌሎች የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች ኃላፊነቱን ወስደው እንዲሰሩ አሳስበዋል፡፡
በምረቃው ስነ ስርዓቱ የህትመት ሚዲያ ታላቅነትና የኤልክትሮኒክስ ሚዲያ በንጽጽር በመጽሔቱ ዋና አዘጋጅ በአቶ ምንይችል መሰረት ቀርቦ የአምድ ተሳታፊዎችን ከፍ ለማድረግም አጭር ውይይት ተካሂዶና አስተያየት ተሰጥቶበት መርሃግብሩ ተጠናቋል፡፡
የኮሌጁን የምርምር፣ የመማር ማስተማር ስራዎችና የማህበረሰብ አገልግሎት አበይት ክንውኖችን በመጠናዊ ዜና ማስተዋወቅና መሰነድ፣ መምህራንና ተማሪዎች ያላቸውን ግንኙነት ዘርፈ ብዙ እንዲሆን መምከርና ማጠናከር፣ መምህራን በንባብና በምርምር ያገኟቸውን እውቀቶች የሚያካፍሉበት መድረክ ሆኖ ማገልገልን አላማ ያደረገ ሰበዝ የተሰኘች መጽሔትን ባለፍው 2013ዓ/ም ዕትም አንድን ማስመረቁ የሚታወቅ ነው፡፡
**************************************************
ለልህቀት እንተጋለን!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ሰኔ 29/2014 ዓ.ም