በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ የፓለቲካል ሳይንስና አስተዳደር ጥናት ትምህርት ክፍል አዘጋጅነት በፓለቲካል ሳይንስ የሶስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ለመክፈት ምሁራንን ያሳተፈ የውጭ ስርዓተ-ትምህርት ግምገማ አውደ-ጥናት /External Curriculum Review Workshop/ ነሀሴ 27/2014 ዓ.ም በማራኪ ግቢ በአልሙኒየም መሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ።
ዩኒቨርሲቲው የምርምር የልዕቀት ማዕከል ለመሆን የሚያደርገውን ጥረት ለማሳካት የድህረ-ምረቃ ፕሮግራሞችን ማስፋፋት አስፈላጊ መሆኑን የገለፁት የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ-ሰብዕ ኮሌጅ ም/ዲን ዶ/ር አዕምሮ አስማማው፤
የሀገራችን የፖለቲካ አቅም በበሰለ መልኩ ሳይንሱንና ቲዎሪውን ተመርኩዞ የፖለቲካል ሳይንሱን በፖለቲካል ቲዎሪ ሌንስ ለማየት ማስቻል መሆኑን ተናግረዋል።
በእለቱ በተካሄደው የስርዓተ-ትምህርት ግምገማ በዩኒቨርሲቲያችን የሚገኙ ምሁራን፣ ከአዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ (በበይነ-መረብ)፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (በበይነ-መረብ) በትምህርት ክፍሉ የተሻለ እውቀትና ልምድ ያላቸው ምሁራን ለስርዓተ-ትምህርቱ ግብአት የሆኑ የተለያዩ ምክረ ሀሳቦች አቅርበዋል፡፡
በመጨረሻም ከምሁራኑ የተሰጡትን ምክረ-ሀሳቦች በማካተት የተሻለ ሰርዓተ- ትምህርት ለመተግበር አውደ-ጥናቱ መካሄዱን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፓለቲካል ሳይንስና አስተዳደር ጥናት ትምህርት ክፍል ሃላፊ ዶ/ር ባምላክ ይደግ ገልፀዋል።
***********************************
ለልህቀት እንተጋለን!
የህዝብና ዓለም ዓቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ነሀሴ 27/2014 ዓ.ም
3 Comments
Introducing to you the most prestigious online entertainment address today. Visit now to experience now! Website: https://8kbet.navy/
หวยออนไลน์เป็นหนึ่งในรูปแบบการเดิมพันที่ได้รับความนิยมอย่างมากในปัจจุบัน ด้วยความสะดวกสบายที่ผู้เล่นสามารถเข้าถึงได้ทุกที่ทุกเวลา การซื้อหวยผ่านระบบออนไลน์ช่วยให้คุณไม่ต้องเดินทางไปยังร้านค้าหรือจุดขาย อีกทั้งยังมีหลากหลายรูปแบบให้เลือกเดิมพันตามความชอบ
heylink.me/officialziatogel888